12ኛ ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀመራል - ኢዜአ አማርኛ
12ኛ ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀመራል
የካቲት 2/2014/ኢዜአ/ የ2014 የውድድር ዘመን 12ኛ ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጀመራል፡፡
የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በተመረጡ ከተሞች እየተካሄደ ሲሆን፤ ከ10ኛ ሳምንት ጀምሮ ያሉ ጨዋታዎች ደግሞ በድሬደዋ ከተማ አስተናጋጅነት እየተካሄዱ ይገኛሉ፡፡
በዚህም የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ 12ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ እስከ ቀጣዩ ቅዳሜ ድረስ የሚደረጉ ይሆናል።
በዛሬው መርሃ ግብር ፋሲል ከነማ ከአዳማ ከተማ ከቀኑ 10 ሰዓት እንዲሁም ሀድያ ሆሳዕና ከሰበታ ከተማ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
ፋሲል ከነማ ዛሬ ማሸነፍ ከቻለ የደረጃ ሰንጠረዡን የመሪነት ቦታ ከቅዱስ ጊዮርጊስ የሚረከብ ይሆናል።
ፕሪምየር ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ23 ነጥብ፣ ፋሲል ከነማ በ21 ነጥብ እንዲሁም ሀዋሳ ከተማ በ20 ነጥብ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ እየመሩ ይገኛሉ፡፡