ቀጥታ፡

የናይጄሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ኮምቦልቻ ከተማ ገቡ

ጥር 30/2014/ኢዜአ/ የናይጄሪያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ አሸባሪው ህወሓት በከፈተው ጦርነቱ የደረሰውን ጉዳት ለመመልከት ኮምቦልቻ ከተማ ገቡ።

ኦባሳንጆ ኮምቦልቻ ከተማ ሲገቡ የአማራ ክልል አመራሮችና የተለያዩ አካላት በኮምቦልቻ አየር ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱ ሁሴን ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ኦባሳንጆ በቆይታቸው  አሸባሪው ህወሓት በጦርነቱ ያደረሰውን ኢ-ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ይመለከታሉ ብለዋል።

በሽብር በድኑ የወደሙ የህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ከጎበኙ በኋላ ከአመራሩ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ገልጸዋል።

እንደ ዋና አስተዳዳሪው ገለጻ የሽብር ቡድኑ በዞኑ ተቋማትን ከመዝረፍና ከማውደም ባለፈ በንጹሀን ዜጎች ላይም ዘግናኝ ግፍና መከራ ፈጽሟል።

"የጥፋት ቡድኑ በክልሉ ስላደረሰው ሁለተናዊ ውድመትና ጥቃትም ለኦባሳንጆ ገለጻ ይደረግላቸዋል" ብለዋል።

ከእዚህ በተጨማሪም ኦባሳንጆ በደሴ ከተማም ከአመራሩና ባለድርሻ አካላት ጋር የጉብኝትና የውይይት መድረክ ይኖራቸዋል ተብሎም እንደሚጠበቅም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም