የዓለም ጤና ድርጅት በኮንጎ ኢቦላ እየተስፈፋ መሆኑን ተከትሎ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ

153
ግንቦት 10/2010 በኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የኢቦላ ወረርሽኝ እየተስፋፋ በመምጣቱ በስጋቱ ላይ ለመምከር የዓለም ጤና ድርጅት አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል። እንደ አዲስ በተቀሰቀሰው ወረርሽኝ እስካሁን 44 ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁ ሲሆን፥ 23 ሰዎችም ሞተዋል። በገጠር አካባቢ የተከሰተው ወረርሽኝ አሁን ወደ ከተሞችም እየተስፋፋ ነው ተብሏል። በምባንዳካ ከተማ በሽታው መከሰቱ የተረጋገጠ ሲሆን፥ 1ሚሊየን ሰዎች የሚኖሩባት ይህች ከተማ የትራንስፖርት ማዕከልም በመሆኗ ወረርሽኙ ሊስፋፋ ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል። የሀገሪቱ ዋና ከተማ ኪኒሻሳ እና ጎረቤት ሀገራትም ስጋት ውስጥ መሆናቸው ነው የተነገረው። በኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ለተቀሰቀሰው የኢቦላ ወረርሽኝ ምላሽ ለመስጠት የዓለም ጤና ድርጅት የላካቸው 4 ሺህ ክትባቶች በስፈራው የደረሱ ሲሆን፥ ተጨማሪ ክትባት በቅርቡ እንደ ሚላክ ይጠበቃል። የዓለም ጤና ድርጅት የጤና ባለሙያዎች እስካሁን በበሽታው ከተጠቁት ጋር ንክኪ ይችላሉ በሚል 430 ሰዎችን ለይተዋል። ኢቦላ ከፈረንጆቹ 2014-2016 ባሉት ዓመታት በምዕራብ አፍሪካ ጊኒ ሴራልዮን እና ላይቤሪያ በተቀሰቀሰበት ወቅት ከ11 ሺህ በላይ ሰዎች ሞተዋል። በወቅቱ የዓለም ጤና ድርጅት ምላሽ ለመስጠት መዘግየቱን ማመኑ ይታወሳል። ምንጭ፦ቢቢሲ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም