በርካታ የአፍሪካ አገራት መሪዎች በህብረቱ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ እየገቡ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በርካታ የአፍሪካ አገራት መሪዎች በህብረቱ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ እየገቡ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 28 ቀን 2014 (ኢዜአ) በርካታ የአፍሪካ አገራት መሪዎች በህብረቱ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ እየገቡ ነው።
ዛሬው እለት ከማለዳው ጀምሮ የኤስዋቲኒ፣ የኬፕ ቨርዴ ፣ የሞዛምቢክና የጅቡቲ እና የኬኒያ መሪዎች አዲስ አበባ ገብተዋል።
የኤስዋቲኒ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የኬፕ ቨርዴ ፣ የሞዛምቢክ፣ የጂቡቲ እና የኬኒያ ፕሬዚዳንቶች አዲስ አበባ ገብተዋል።
የኤስዋቲኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲፖ ድላሚኒ፣ የኬፕ ቨርዴ ፕሬዚዳንት ጆዜ ማሪያ ኔቪሽ፣ የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንት ክቡር ፊሊፕ ኒየሲ፣ የጂቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኡመር ጌሌህ፣ የኬኒያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አዲስ አበባ ገብተዋል።
የአገራቱ መሪዎች ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የአፍሪካ ህብረት 35ኛው የመሪዎች ጉባኤ የአፍሪካ አህጉርን የስርዓተ ምግብ አቅም መገንባት፤ የሰው ሃብት ልማት፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማትን ያፋጥናል'' በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ ተጀምሯል።