ቀጥታ፡

አዲስ አበባ በመልካም እንግዳ ተቀባይነት አስተናግዳናለች - ጋዜጠኛ ቤቱል ሞኖቪኖሉ

ጥር 27 ቀን 2014 (ኢዜአ) አዲስ አበባ ሰላማዊና ውብ ሆና በመልካም እንግዳ ተቀባይነት አስተናግዳናለች ስትል ቱርካዊቷ ጋዜጠኛ ቤቱል ሞኖቪኖሉ ተናገረች፡፡

የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤትና የመሪዎች ጉባኤን ለመዘገብ ወደ አዳስ አበባ የመጣችው ቱርካዊቷ የሲጂቲኤን አፍሪካ ጋዜጠኛ ቤቱል ሞኖቪኖሉ ከኢዜአ ጋር በነበራት ቆይታ በኢትዮጵያ ያየችው ሰላማዊ እንቅስቃሴና የህዝቡ እንግዳ ተቀባይነት እንዳስገረማት ተናግራለች።

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ችግር እንዳለ ሲነገር እንደነበር አስታውሳ፤ እርሷ የታዘበችው ፍጹም የተለየ መሆኑን ገልጻለች።

አዲስ አበባ ስትደርስ ከተማዋ ፍጹም ሰላማዊና ውብ ሆና እንዳገኘቻት የተናገረችው ጋዜጠኛዋ፤ ህዝቡም በመልካም መስተንግዶ ተቀብሎናል ስትል ገልጻለች።

አዲስ አበባ ደህንነቷ የተጠበቀ ከተማ በመሆኗ በምሽትም ጭምር በነጻነት መንቀሳቀስ ችለናል ስትል ተናግራለች።

ጓደኞቿ ኢትዮጵያን እንዲጎበኙና ልዩ ልዩ መገለጫዎቿን መጥተው እንዲመለከቱ እንደምትጋብዛቸውም ተናግራለች።

በኢትዮጵያ ጉዳይ የተሳሰተ መረጃ ማሰራጨት ተገቢነት የሌለው ነው ብላለች።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም