ቀጥታ፡

የሞሪታኒያው ፕሬዚዳንት መሀመድ ወልደ ሼህ አልገዘዋኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጥር 27 ቀን 2014 (ኢዜአ) ከነገ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በሚካሄደው 35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የሞሪታኒያው ፕሬዚዳንት መሀመድ ወልደ ሼህ አልገዘዋኒ አዲስ አበባ ገቡ።

ኘሬዚዳንቱ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የአገር መከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሀም በላይ እና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ አቀባበል አድገውላቸዋል።

May be an image of 8 people, people standing and outdoors

የአቀባበል ስነ-ስርዓቱ በመከላከያ ማርች ባንድ እንዲሁም በኢትዮጵያና በሞሪታኒያ የባህል ውዝዋዜና በሰርከስ ትርኢት የደመቀ ነበር።

በህብረቱ ጉባኤ ለመሳተፍ የተለያዩ አፍሪካ አገሮች መሪዎች ከትናንት ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ እየገቡ መሆኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም