ቀጥታ፡

ኢትዮጵያዊያን በደቡብ አፍሪካ እየተፈጸመ ካለው ጥቃት ራሳቸውን እንዲጠብቁ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ ነሃሴ 25/2010 ኢትዮጵያዊያን በደቡብ አፍሪካ ስዌቶ የሌላ አገር ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ካለው ጥቃት ራሳቸውን እንዲጠብቁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ። በእስካሁኑ ጥቃት አንድ ኢትዮጵያዊ ህይወቱ ሲያልፍ ሌላ ኢትዮጵያዊ ደግሞ ጉዳት ደርሶበት ህክምና ላይ ይገኛል። ደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከአገሪቱ መንግስት ጋር በመሆን በዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለማስቆም እየሰራሁ ነው ብሏል። መረጃ ለምትፈልጉ ኢትዮጵያዊያንም በስልክ ቁጥሮች 0123462110 እና 0123462947 መደወል እንደምትችሉ ገልጿል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም