40ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ ተጀምሯል

57

ጥር 25 ቀን 2014 (ኢዜአ)40ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ ተጀምሯል።

በጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት "በአፍሪካ በየአቅጣጫው እያጋጠመ ያለውን የተለያዬ ቅርፅ የያዘውን የሰላም እና ፀጥታ ችግር ለመፍታት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባል"ብለዋል።

የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ይህን ያሉት 40ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ ሲጀመር ባደረጉት ንግግር ነው።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ክቡር ሙሳ ፋኪ መሃመትየኮሮና ቫይረስ የፈጠረው ተፅዕኖ እና ለመቋቋም እየተደረገ ስላለው ጥረት፣የአጀንዳ 2063 የአፈጻጸም ሂደት፣የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና አተገባበር እንቅስቃሴ እና መሰል ወቅታዊ የአህጉሪቷን አጀንዳዎች አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም