በሆሳዕና የኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ አደባባይ ሀውልትና የሊች ጎጎ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
በሆሳዕና የኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ አደባባይ ሀውልትና የሊች ጎጎ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ
ሆሳዕና ጥር 22/2014(ኢዜአ) በሆሳዕና ከተማ ከ220 ሚሊየን ብር በላይ የተገነባው የጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ መታሰቢያ አደባባይ ሃውልትና የሊች ጎጎ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ህንፃ ምረቃ ስነ ስርአት ተካሄዷል ።
የአደባባይ ሀውልቱና ትምህርት ቤቱ የተገነባው በሀድያ ልማት ማህበር አማካኝነት ነው።
በተጨማሪም በከተማው በ700 ሚሊዮን ብር እየተገነባ የሚገኘው የህዝብ መዝናኛ ፓርክ የጉብኝት ስነ ስርአትም እየተካሄደ ነው ።
በከተማው መሰረተ ልማት ማስፋፋት የጎላ አስተዋፅኦ ለነበራቸውና በአደዋ ጦርነት ታላቅ ተጋድሎ ላበረከቱት ለፊት አዉራሪ ጌጃ ጌሪቦ መታሰቢያ የአደባባይ ሀውልት ማስጀመሪያ የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ ስርአትም እየተካሄደ ነው።
በመርሐ ግብሩ ላይ የኢፌዴሪ አየር ሀይል ዋና አዣዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳን ጨምሮ የፌዴራል፣ የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ አርቲስቶችና ታዋቂ ግለሰቦች ተገኝተዋል።