ወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን ከዳያስፖራዎች ጋር በመተባበር ያሳደሳቸውን የአረጋዊያን ቤቶች ለነዋሪዎች አስረከበ - ኢዜአ አማርኛ
ወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን ከዳያስፖራዎች ጋር በመተባበር ያሳደሳቸውን የአረጋዊያን ቤቶች ለነዋሪዎች አስረከበ
ጥር 21 ቀን 2014 (ኢዜአ) ወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን ከዳያስፖራዎች ጋር በመተባበር ያሳደሳቸውን የአረጋዊያን ቤቶች ለነዋሪዎች አስረከበ፡፡
ፋውንዴሽኑ ዛሬ ያስረከባቸው ቤቶቸ 15 ሲሆኑ፤ ለ40 ዓመታት ያህል ሳይታደሱ የቆዩና ለኑሮ ምቹ ያልነበሩ መሆናቸው ታውቋል፡፡
በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይም የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር መሀመድ እድሪስ እና የእስልምና ሃይማኖት መምህር ኡስዝታዝ አቡበከር አህመድን ጨምሮ ዳያስፖራዎች ተገኝተዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት ዳያስፖራዎች ወንድም ካሊድ ፋውንዴሽንን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼