በ550 ሚሊዮን ዶላር የሚተገበረው የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔትና ስራ ፕሮጀክት ትግበራ ነገ በይፋ ይጀመራል

93

ድሬዳዋ፣ ጥር 20 ቀን 2014 (ኢዜአ) በሀገር አቀፍ ደረጃ በ550 ሚሊዮን ዶላር ተግባራዊ የሚደረገው ሁለተኛው ምዕራፍ የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔትና ስራ ፕሮጀክት ነገ በይፋ እንደሚጀመር የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ፕሮጀክቱ 'ልማታዊ ሴፍቲኔት ለከተሞች ሁለንተናዊ ለውጥ' በሚል መሪ ሃሳብ ነገ በአገር አቀፍ ደረጃ ድሬዳዋ ላይ በይፋ ይጀመራል።

በሚኒስቴሩ የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔትና ሥራ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ መኮንን ያኢ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ፕሮጀክቱ በአገሪቱ በተመረጡ 83 ከተሞች ተግባራዊ ይደረጋል።

ፕሮጀክቱ በዓለም ባንክና በኢትዮጵያ መንግሥት 550 ሚሊዮን ዶላር በጀት የሚተገበርና 816 ሺህ 500 ዜጎችን በቀጥታና በልማት ስራዎች በማሳተፍ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ነገ በይፋ በሚጀመው ፕሮጀክት ስነ ስርአት ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም