ቀጥታ፡

በአውሮፕላን አደጋ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ዓለም አቀፍ አውደ ጥናት ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ ነሃሴ 24/2010 የአውሮፕላን አደጋ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ዓለም አቀፍ አውደ ጥናት ሊካሄድ መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን አስታወቀ። አውደ ጥናቱ 'መሰረታዊ የአውሮፕላን አደጋ ስጋት፣ የምርመራ ዘዴዎችና የማሻሻያ ሀሳቦች' በሚል መሪ ቃል ከነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜን 3 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚ ይካሄዳል። በአውደ ጥናቱ የአገር ውስጥ ባለድርሻዎችና የውጭ ባለሙያዎችን ጨምሮ 80 ተሳታፊዎች እንደሚኖሩ ሲጠበቅ በአውሮፕላን አደጋ ምርመራ፣ መሠረታዊ መርሆችና ተመራጭ አሰራሮች ዙሪያ ምክክር ይደረጋል ተብሏል። እንዲሁም አገራት በዓለም አቀፍ የአደጋ ምርመራ የማረጋጋጫ ዘዴ የሚከተሉበትን ጠቋሚ ጽንሰ ሀሳቦችም ይዳሰሳሉ። በኢትዮጵያ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪን ዕድገት መነሻ በማድረግ ደህንነቱ የተጠበቀ ዓለም አቀፍ ግዴታን የሚወጣ የአውሮፕላን አደጋ ምርመራ ቢሮ በአዋጅ ተቋቁሟል። ቢሮው በአፍሪካ የአውሮፕላን አደጋ ምርመራ ቀዳሚ በመሆን እየሰራ ሲሆን የአውሮፕላን አደጋ መከላከል ደህንነት ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ አባል ሆኖ ለዘርፉ መሻሻል የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን አስታውቋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም