የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተቋማት ላይ የመስክ ምልከታ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተቋማት ላይ የመስክ ምልከታ አደረገ
ጥር 17 ቀን 2014 (ኢዜአ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተቋማት ላይ የመስክ ምልከታ አደረገ።
ምልከታ የተደረገባቸው ተቋማት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ጤና አገልግሎት ዋና መምሪያና የወንጀል ምርመራ ቢሮ ናቸዉ።
የቋሚ ኮሚቴው አባላት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ጤና አገልግሎት ዋና መምሪያ የሚሰጣቸው አገልግሎት፣ አደረጃጀትን ጨምሮ ስለ አጠቃላይ አገልግሎቱ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
የበጀት እጥረት፣ የመድሃኒትና ለህሙማን የምግብ በጀት አጥረት፣ የህክምና መስጫና ለቢሮ የሚሆኑ ክፍሎች ችግርና ሌሎች ሆስፒታሉን እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለቋሚ ኮሚቴው አስረድተዋል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ እጸገነት መንግስቱ በተነሱት ችግሮች ዙሪያ ከሚመለከታቸው ጋር እንደሚነጋገሩ ገልጸዋል።
ቋሚ ኮሚቴው በሆስፒታሉ ህክምና እየተከታተሉ የሚገኙ የሰራዊት አባላትን ጉብኝተዋል።
በፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮም በተመሳሳይ የተጠርጣሪዎችን ሰብአዊ መብት አያያዝ፣ የምርመራ ሂደትን ጨምሮ አጠቃላይ በወንጀል ምርመራ የመጡ ለውጦች ላይ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
ቋሚ ኮሚቴው በወንጀል ምርመራ ቢሮ የሚገኙ ተጠርጣሪዎችን ጎብኝተዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼