ቀጥታ፡

የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ኮሚሽነሮች

በሙሳ ፋቂ ማሃማት ሊቀመንበርነት የሚመራው የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን በስሩ ስድስት ኮሚሽኖች አሉት። እነሱም:-

1. የ’ግብርና ገጠር ልማት ብሉ ኢኮኖሚና ዘላቂ ከባቢ አየር’ ኮሚሽን - በአንጎላዊቷ ጆሴፋ ሳኮ የሚመራ፤

2.  የኢኮኖሚ ልማት፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ኮሚሽን - በዛምቢያዊው አልበርት ሙቻንጋ የሚመራ፤

3.  የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽን - በካሜሮናዊቷ ፕሮፌሰር ሳራ አንያንግ አግቦር የሚመራ፤

4.  የመሰረተ ልማትና ኢነርጂ ኮሚሽን - በግብጻዊቷ አማኒ አቡ-ዘይድ የሚመራ፤

5.  የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ደህንነት ኮሚሽን - በናይጄሪያዊው አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ የሚመራ፤

6.  የጤና፣ ሰብአዊ ጉዳዮችና የማህበራዊ ልማት ኮሚሽን - በሱዳናዊቷ አሚራ ኤል ፋዲል የሚመራ፤

ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ኮሚሽነሮች መካከል አራቱ ሴቶች ናቸው።

አንድ ኮሚሽነር ለአራት ዓመት የሚያገለግል ሲሆን ኮሚሽነር ለመሆን በሚደረግ ምርጫ በድጋሚ ለመመረጥ መወዳዳር ይችላል።

የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የሆኑት የቻድ ዲፕሎማት ሙሳ ፋቂ ማህማት እ.አ.አ በ2021 የካቲት ወር ላይ በተካሄደ ምርጫ ለአራት ዓመት በሊቀመንበርነት እንዲመሩ ድጋሚ መመረጣቸው ይታወሳል።

ሩዋንዳዊቷ ዶክተር ሞኒክ ንሳንዛባጋንዋ እ.አ.አ በ2021 የመጀመሪያዋ ሴት የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸውም አይዘነጋም።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም