ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጅግጅጋ ገቡ

ጥር 17 ቀን 2014 (ኢዜአ)የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ ጅግጅጋ ገቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከልዑካቸው ጋር ጅግጅጋ ገራድ ዊልዋል አየር ማረፊያ ሲደርሱ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ፣የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የሀገር ሽማግሌዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ልዑካን ቡድኑ በክልሉ በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን በመጎብኘት የሰብዓዊ ድጋፍ ክንውኖችን ይገመግማል።

ምንጭ-የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም