አፄ ምኒልክ በአድዋ ጦርነት የተዋጉበት ጎራዴ ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ

136

ጥር 13 ቀን 2014 (ኢዜአ) አፄ ምኒልክ በአድዋ ጦርነት ላይ የተዋጉበት ጎራዴ ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ።

በወቅቱ ከጎራዴው ጋር ተዘርፎ የነበረው የእንጨት መስቀልም እንዲሁ ተመልሷል።

በተጨማሪም ቀዳማዊ ሐይለስላሴ የተላላኳቸው ደብዳቤዎች፣ ፎቶግራፎች፣ ፖስት ካርዶችና የጽሁፍ እና የምስል ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።

የኢትዮጵያ ቅርስ አስመላሽ ብሔራዊ ኮሚቴ ቅርሶቹን ለቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን አስረክቧል።

የባለስልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ወደ አገር የተመለሱትን ቅርሶች ጠብቆ የማቆየት ሀላፊነትን ተቀብለናል ብለዋል።

ቅርሶቹ በታሪክም የሚነገረውን የኢትዮጵያን ቀደምትነትና ሃያልነት በተግባር የሚያሳዩ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን በተለያየ መንገድ ለማጠልሸት ለሚጣጣሩ አካላት ምላሽ የሚሰጡም ናቸው ብለዋል።

ቅርሶቹን ጠብቆና ተንከባክቦ ከማስቀመጥ ባሻገር በቀጣይ የማስተዋወቅ ስራው እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴን ጨምሮ የማህበሩ አባላትና እንግዶች ተገኝተዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

‼

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም