በእንስሳትና አሳ ሀብት ልማት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው-ቢሮው

ሀዋሳ፤ ጥር 13/2014.(ኢዜአ) በደቡብ ክልል በእንስሳትና እሳ ሀብት ልማት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

የእንስሳትና እሳ ሀብት ልማት ክልል እቀፍ የንቅናቄ መድረክ ዛሬ በእርባ ምንጭ ከተማ ተጀምሯል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ እቶ ኡስማን ስሩር በወቅቱ እንደገለጹት የክልሉን ህዝብ  በእንስሳትና እሳ ሀብት ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተስራ ነው።

በሚሊዮን የሚቆጠሩ አርሶና አርብቶ አደሮችን በዘርፉ በማሳተፍ  በተሰራ ስራ የገቢና የኑሮ ለውጥ ለማምጣት ማስቻሉን ጠቁመዋል።

የተሻሻሉ እሰራሮችን በመጠቀም እንስሳትና አሳ ሀብት ልማትን የገቢ ማስገኛ ማድረግና በዘርፉ የተመዘገቡ ምርጥ ልምዶችን ለማስፋፋት የሚቻልበትን እቅጣጫ ማመላከት የክልል አቀፍ የንቅናቄው መድረክ ዓላማ መሆኑን ገልጸዋል።

በተጨማሪም የዘርፉ ማነቆዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠርና በቀጣይ በየደረጃው የሚገኙ የአመራር እካላትና ተጠቃሚዎች የዘርፉን ፋይዳ በመገንዘብ ርብርብ እንዲያደርጉ ለማስቻል መሆኑን ገልጸዋል።

በቢሮው የእንስሳት ዘርፍ ሃላፊ አቶ እያሱ ተረፈ በበኩላቸው በክልሉ 2 ነጥብ  9 ሚሊዮን የሚሆኑ  የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በእንስሳት ሃብት ልማት  ተጠቃሚ መሆናቸውን አመልክተዋል።

ባለፉት ዓመታት በተለይ ዝርያ ለማሻሻል በተሰራ ስራ የወተት ምርታማነትን በአማካኝ 16 ሊትር ማድረስ መቻሉን ጠቁመዋል።

በሞዴል እርቢዎች ደግሞ ከአንድ ላም በቀን 39 ሊትር ወተት ማግኘት መቻሉን ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት ከ100 ሺህ በላይ የእንስሳት ኤክስቴንሽን ልማት ተሳታፊ አርሶና አርብቶ አደሮች በክልሉ እንዳሉ አስረድተዋል።

አርሶና አርብቶ አደሮች  የተሻሻሉ የወተት  ዝርያ ላሞችን በማርባት እንድ የወተት ላምን ከ60 ሺህ እስከ 120 ሺህ ብር በመሽጥ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ባለፉት ስድስት ወራት በመጀመሪያ ዙር  ከ132 ሺህ በላይ ላሞች ላይ የማዳቀል ስራ መከናወኑን ያመለከቱት ሃላፊው  59 ሺህ 658 ጥጆች መወለዳቸውን አስታውቀዋል።

በዶሮ ልማት ዘርፍም  ከ2 ሚሊዮን የሚበልጡ የአንድ ቀን ጫጩቶችና ከ2 ነጥብ 3 ሚሊዬን በላይ ቄብና የ45 ቀናት ዶሮዎች ለአርሶና አርብቶ አደሮች በማሰራጨት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አብራርተዋል።

 ክልል አቀፉ የእንስሳትና እሳ ሀብት ልማት የንቅናቄ መድረክ ዛሬ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም