ቀጥታ፡

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፍአለ በጎንደር አፄ ፋሲለደስ ጥምቀተ ባህር እየተከበረ ባለው የጥምቀት በዓል ያስተላለፉት መልዕክት በጥቂቱ

ጥምቅት በጎንደር ማክበር ከሃይማኖትና ታሪክ አንጻር ልዩ ውበትና ትርጉም ያለው ነው፣

ጥምቀትን በጎንደር ማክበራችን የማይበገረውና የማይሰበረው የኢትዮጵያ አንድነት ጸንቶ እንደሚቀጥል ለዓለም ለአቀፉ ማህበረሰብ ያሳይንበት ነው፣

ጥምቀትን በጎንደር ማክበር የተቀዛቀዘውን የቱሪዝምና ኢኮኖሚ ለማነቃቃት ያግዛል፣

.ባህላችንና እምነታችንን በነጻነትና በእፎይታ እንድናከብር ላደረጉን የኢትዮጵያ ልጆች ምስጋና ይገባቸዋል፣

ጎንደር ያላትን የቱሪዝም መዳረሻዎች በማልማት በዘርፉ ያለውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የአማራ ክልል መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፣

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ባቀረበችው ጥያቄ መሰረት በጎንደር የጥምቀት በዓል ማክበሪያው ከዛሬ ጀምሮ የአፄ ፋሲለደስ ጥምቀተ ባህር ተብሎ እንዲሰየም የአማራ ክልል መንግስት ወስኗል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም