በ'አይዞን ኢትዮጵያ' ለተፈናቀሉ ዜጎች የተሰበሰበው ገንዘብ ስድስት ሚሊዮን ዶላር ተሻግሯል

74

ጥር 11 ቀን 2014 (ኢዜአ) በ'አይዞን ኢትዮጵያ' የኦንላይን የገንዘብ ክፍያ አማራጭ በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ተሰበሰበ::

ገንዘቡ የተሰበሰበው በውጭ አገር ከሚኖሩ ከ25 ሺህ 140 በላይ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ነው።

ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ የተሰበሰበው ከሶስት ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ መሆኑን ከ'አይዞን ኢትዮጵያ' የክፍያ ድረ ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች ገቢ የሚሰባሰብበት ‘አይዞን ኢትዮጵያ' የኦንላይን የገንዘብ ክፍያ አማራጭ በኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ባለቤትነት የሚመራ ሲሆን፤ የክፍያ አማራጩ ቻፓ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂስ በተሰኘ አገር በቀል ተቋም የለማ ነው።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም