በሰሜን ሸዋ ኢራንቡቲ ስርዓተ ጥምቀቱ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች በድምቀት እየተካሄደ ይገኛል

27

ጥር 11 ቀን 2014 (ኢዜአ) በሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቱም ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቴሌቪዥን ጣቢያ የበላይ ጠባቂ ብጹዕ አቡነ ማቲዎስ፣ ከተለያዩ ደብሮች የተውጣጡ የሃይማኖት አባቶችና የእምነቱ ተከታዮች በመሣተፍ ላይ ይገኛሉ።

የጥምቀት በዓል፣ የኢየሱስ ክርስቶስን በዮርዳኖስ ወንዝ መጠመቅን ለማስታወስ የእምነቱ ተከታዮች በየዓመቱ ጥር 11 ቀን የሚፈጽሙት ስነ-ሥርአት መሆኑ ይታወቃል።

በምንጃር ሸዋ ኢራንቡቲም ይህ የጥምቀት በዓል ዘንድሮ ለ620ኛ እየተከበረ ይገኛል።

በዚህ ቦታ እየተከበረ የሚገኘው የጥምቀት በዓል 44 ታቦታት በአንድ ላይ የሚገኙበት ነው።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም