የከተራ በዓል በኦሮሚያ ክልል ባቱ ከተማ የዝዋይ ደሴቶች ላይ በድምቀት ተከብሯል - ኢዜአ አማርኛ
የከተራ በዓል በኦሮሚያ ክልል ባቱ ከተማ የዝዋይ ደሴቶች ላይ በድምቀት ተከብሯል
ጥር 10 ቀን 2014 (ኢዜአ) ከሦስት የደሴት አድባራት የተነሱ ስድስት ታቦታት ወደ ጥምቀተ ባህር የማደሪያ ስፍራቸው ገብተዋል።
ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የመጡ ምዕመናንና ጎብኚዎች በከተራ በዓሉ ላይ ታድመዋል።
በባህር ላይ የተለያዩ ትዕይንቶች የታጀበው የታቦታቱ ሽኝት የበዓሉን ተሳታፊዎች ቀልብ የሳበ ነበር።