ቀጥታ፡

ለተፈናቀሉ ዜጎች በተካሄደ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ከ800 ሺህ ዶላር በላይ ተሰበሰበ

ጥር 09 ቀን 2014 (ኢዜአ) ለተፈናቀሉ ዜጎች በተካሄደ የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት መርሃ ግብር ከ800 ሺህ ዶላር በላይ መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ።

ትናንት በታላቁ ቤተ-መንግስት በተካሄደው የእራት መርሃ ግብር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ(ዶ/ር፣ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የዳያስፖራ አደረጃጀት መሪዎች፣ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ተገኝተዋል።

ከእራት ግብዣው አስቀድሞ በ’አይዞን ኢትዮጵያ’ የበይነ መረብ የገንዘብ ክፍያ አማራጭ አስቀድሞ በተካሄደ የትኬት ሽያጭ በቀጥታ ከ800ሺህ ዶላር በላይ ገቢ መደረጉን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ገልጿል።

የትናንቱ መርሃ ግብር የኢትዮ-ካናዳውያን ኔትወርክ ለማህበራዊ ድጋፍ(ኢክናስ)፣ጌትፋክት፣ ‘አሜሪካን ኢትዮጵያ ፐብሊክ አፌርስ ኮሚቴ’(ኤፓክ) እና ግሊን የተሰኙ በአሜሪካና በካናዳ የሚገኙ ተቋማት ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ጋር በመተባባር ያዘጋጁት እንደሆነም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም