በደቡብ ኦሞ ዞን ቶልታ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በ11 መኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት ደረሰ

458

ጂንካ፣ ጥር 08 ቀን 2014 (ኢዜአ) በደቡብ ኦሞ ዞን ቶልታ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በ11 መኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ።

የዞኑ  ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ዮሐንስ መኮንን ለኢዜአ እንደገለጹት፤  ትናንት እኩለ ሌሊት ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ የስድስት ዓመት ዕድሜ ያላት ህፃን ህይወቷ አልፏል።

በአደጋው  ዘጠኝ  መኖሪያ ቤቶች  ሙሉ በሙሉ መውደማቸውና  በሌሎች ሶስት ቤቶች ላይ ደግሞ  መጠነኛ ጉዳት መድረሱን አስታውቀዋል።

የአደጋው መንስኤ  እየተጣራ መሆኑን ኢንስፔክተር ዮሐንስ ገልጸዋል።

የዞኑ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደሞ በዛብህ  የአካባቢውን ማህበረሰብ በማሳተፍ በተደረገው ርብርብ አደጋው የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር እንደተቻለ ተናግረዋል።

ማህበረሰቡ ላደረገው ትብብርም ምስጋና አቅርበዋል።

ቶልታ ከተማ በደቡብ አሪ ወረዳ የምትገኝ ከተማ ስትሆን፤ ከጂንካ በ39 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች። 

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም