ቀጥታ፡

በህልውና ዘመቻው የተሳተፉ አትሌቶች በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን የጉባዔ አባላት እውቅና ተሰጣቸው

አዲስ አበባ፣ ጥር 6/2014 (ኢዜአ)  የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 25ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ነዉ።

በዚህ ጉባዔ የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጀላ መርዳሳ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉና የጉባኤው አባላት በተገኙበት እየተካሄደ ነው ።

በህልውና ዘመቻዉ ከተሳተፉ አባላት መካከል አትሌት ገዛኸኝ አበራ፣ ኮማንደር ማርቆስ ገነቴና ዋና ኦፈሰር ፋንቱ ሚጌሶ ዋንጫ ተሸልመዋል።

ሻለቃ ሐይሌ ገብረ ስላሴ እና ፈይሳ ሌሊሳም በስራ መደራረብ በቦታው ባይገኙም በጉባኤው አባላት እውቅና ተሰቷቸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም