ቀጥታ፡

በምስራቅ መስቃን ቤተ ጉራጌ እና በማረቆ ወረዳ ማህበረሰብ መካከል የእርቅ ስነ-ስርዓት እየተካሔደ ነው

ጥር 5 ቀን 2014 (ኢዜአ) በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን በምስራቅ መስቃን ቤተ ጉራጌ እና በማረቆ ወረዳ ማህበረሰብ መካከል የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት በሁለቱም ወገን የሀገር ሽማግሌዎች የእርቅ ስነ-ስርዓት በመካሄድ ላይ ነው።

በሁለቱ ህዝቦች መካከል ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ዛሬ በኢንሴኖ ከተማ ባህላዊ የእርቅ ስነ ስርዓት እየተካሔደ ይገኛል።

በባህላዊ የእርቅ ስነ ስርዓቱ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የክልል እና የዞን የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም