ቀጥታ፡

በቀጠናው የሰላምና የመከባበር ዕሴትን ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

ጥር 4 ቀን 2014 (ኢዜአ) በምሥራቅ አፍሪካ የቀጠናውን የሰላምና የመከባበር ዕሴት ለመገንባት እንዲሁም ጽንፈኝነትን ለመከላከል የሚያስችል ስምምነት ተካሄደ።

ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤና የኬኒያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ናቸው።

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ የስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላትና የኬኒያ የተቋሙ ዳይሬክተርና ዋና ጸሐፊ ተፈራርመዋል።

ይህ ስምምነት ለአገራዊና አካባቢያዊ ሰላምና ጸጥታ መጠበቅ የላቀ ፋይዳ ይኖረዋልም ተብሏል።

ስምምነቱ የሁለቱ ሀገራት በጋራና በትብብር የመስራት አካል ነው የተባለ ሲሆን ወደፊትም በቀጠናው ካሉ አገራት ጋር ይህ ግንኙነት እንደሚጠናከር ተጠቁሟል።

ከዚህም በተጨማሪ ስምምነቱ ትውልድን በበጎ ለመገንባትና የዕርቀ ሰላም አጀንዳዎችን ለማስፈጸም እንደሚያስችል ነው የተነገረው።ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ

‼️

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼️

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼️

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼️
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም