ዳያስፖራው በቴክኖሎጂ ዘርፍ ባለው ልምድና እውቀት ሀገሩን እንዲደግፍ ጥሪ ቀረበ

64

ጥር 3 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ታላቁን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ጥሪን ተቀብለው ወደ ሀገራቸው የመጡ ዳያስፖራዎች ሀገራቸውን በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ እንዲደግፉ ጥሪ አቅርቧል።

ሚኒስቴሩ ዳያስፖራዎች በዘርፉ ሀገራቸውን ለመደገፍ እና የኢንቨስትመንት አማራጮችን ማየት በሚቻልበት ጉዳይ ላይ በመጪው ሃሙስ ይመክራል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ፥ የግሉን ዘርፍ እና የዳያስፖራውን አባላት ተሳትፎ የሚያጠናክር ፎረም በእለቱ እንደሚመሰረት ተናግረዋል።

ዳያስፖራው ኢትዮጵያ ላይ የሚደርሰውን አለም አቀፍ ጫና በመቃወም ያስመዘገበውን ውጤት ያደነቁት ሚኒስትር ዴኤታዋ ፥በቴክኖሎጂው ዘርፍም ይህንን ታሪክ እንዲደግመው ጥሪ አቅርበዋል።

በመጪው ሃሙስ በሚካሄደው የምክክር መድረክ በዘርፉ ሀገራቸውን መደገፍ የሚችሉ ሁሉ እንዲሳተፉ ጥሪ መቅረቡን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም