ፊልድ ማርሻል ብርሐኑ ጁላን ጨምሮ አራት ጀኔራል መኮንኖች ወደር የሌለለው የጥቁር አንበሳ ጀግና ሜዳይ ተሸለሙ - ኢዜአ አማርኛ
ፊልድ ማርሻል ብርሐኑ ጁላን ጨምሮ አራት ጀኔራል መኮንኖች ወደር የሌለለው የጥቁር አንበሳ ጀግና ሜዳይ ተሸለሙ
ጥር 01 ቀን 2014 (ኢዜአ) ፊልድ ማርሻል ብርሐኑ ጁላን ጨምሮ አራት ጄኔራል መኮንኖች ወደር የሌለለው የጥቁር አንበሳ ጀግና ሜዳይ ተሸለሙ።
በዛሬው ዕለት በተደረገው የዕውቅናና የሽልማት መድረክ አራት ጀኔራል መኮንኖች በምርጥ ወታደራዊ አመራርነት ሚናቸው ከፍተኛውን ብሔራዊ ሽልማት ተቀዳጅተዋል።
በዚህም ጀኔራል መኮንኖቹ ጠቅላይ ኢታማዦ ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ ምክትል አታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሰ፣ ጀኔራል ባጫ ደበሌ እና ሌተናል ጀኔራል አለምእሸት ደግፌን ናቸው።
ጀኔራል መኮንኖቹ በአገር የማዳን የሕልወና ዘመቻም ሆነ እና ከዛም በፊት የነበራቸው አኩሪ ጀብዱ፣ ገድልና ታሪካቸው ተወስቶ ወደር የሌለው የጥቁር አንበሳ ጀግና ሜዳይ ሽልማትን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዕጅ ተረክበዋል።