አዲሱ የመከላከያ ሚኒስቴር ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት በመካሄድ ላይ ነው - ኢዜአ አማርኛ
አዲሱ የመከላከያ ሚኒስቴር ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት በመካሄድ ላይ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 01 ቀን 2014 (ኢዜአ) እጅግ ዘመናዊ እንደሆነ የተነገረለት የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ በተገኙበት እየተካሄደ ነው።
ህንጻው በ13 ሺህ ካሬ ላይ ያረፈው ባለ 5 ወለል ሲሆን ከ700 በላይ ቢሮዎችና የተለያየ ደረጃ ያላቸው የስብሰባ አዳራሾች፣ ቤተ-መጽሐፍት፣ የምርምር ማዕከላት እና የተደራጀ የመረጃ ማዕከል በውስጡ ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።
በዚህ የምረቃ ሥነ-ሥርዓተ ላይ ምድር ጦር እና አየር ኃይል ወታደራዊ ትዕይንት በማሳየት ላይ ናቸው።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት እና ወታደራዊ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ