ቀጥታ፡

የገና እና የጥምቀት በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ፖሊስ ከወጣቶች ጋር በመቀናጀት እየሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27 ቀን 2014 (ኢዜአ)የገና እና የጥምቀት በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ፖሊስ ከወጣቶች ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ፤ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ፖሊስ ከከተማዋ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ጋር በመቀናጀት የመዲናዋን ሰላም እያሰጠበቀ መሆኑን ተናግረዋል።

ለገና እና ለጥምቀት በዓላት ሰላማዊነት ደግሞ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከተለያዩ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ዳያስፖራዎችና የኢትዮጵያ ወዳጆችም በመዲናዋ የትኛውም አካባቢ ሲንቀሳቀሱ የጸጥታ ችግር እንዳይገጥማቸው ፖሊስ የተጠናከረ ክትትልና ጥበቃ እያደረገ መሆኑን ኮማንደር ፋሲካ ገልጸዋል።

በዓሉ በሰላምና በደስታ እንዲጠናቀቅ አሽከርካሪዎችም ሆኑ እግረኞች በሃላፊነት ስሜት ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ

‼️

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼️

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼️

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼️

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም