ጄፍሪ ፌልትማን ከአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛነታቸው ሊነሱ ነው

100

ታህሳስ 27 ቀን 2014 (ኢዜአ) በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው በማገልገል ላይ ያሉት ጄፍሪ ፌልትማን ከኃላፊነታቸው እንደሚነሱ ታወቀ።

በቱርክ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ተሰናባቹ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ እንደሚተኳቸውም የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል።

ፌልትማን ላለፉት ዘጠኝ ወራት በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ ልዑክ ሆነው እንደሚሾሙ የሚጠበቁት አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ከ40 ዓመታት በላይ ልምድ ያላቸው አንጋፋ ዲፕሎማት ናቸው።

ቀደም ሲልም በሳውዲ ዓረቢያ፣ ሊባኖስ፣ ቱኒዚየ እና ሶሪያ በዲፕሎማትነት ያገለገሉ ሲሆን በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤትም የመካከለኛው ምሥራቅ ጉዳዮች ከፍተኛ ዲፕሎማት ሆነው ማገልገል ችለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም