ለኢትዮጵያ የምንችለውን ሁሉ ማድረግ አለብን-ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ

ታህሳስ 27 ቀን 2014 (ኢዜአ)ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ያቀረቡትን የታላቁ ወደ ሀገር ቤት ጉዞ በመቀበል ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብታለች።

ጋዜጠኛዋ ለኢትዮጵያ የምንችለውን ሁሉ የማድረግ ግዴታ አለብን ስትል ጥሪ አቅርባለች።

ጋዜጠኛ ሄርሜላ አዲስ አበባ የገባችው ከወላጅ እናቷ ጋር ሲሆን ቦሌ አለማቀፍ አየር አውሮፕላን ማረፊያ ስትደርስም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰሜን፣ ደቡባዊ አሜሪካና የካሪቢያን ሀገራት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ዶ/ር ገበየሁ ጋንጋን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች አቀባበል አድርገውላታል።

ኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለውን ያልተገባ ጫና በመቃወም የምትታወቀው ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ የተደረገላት አቀባበል እንዳስደሰታት ተናግራለች።

የኢትዮጵያን ምድር ከረገጥኩኝ ጀምሮ የተሰማኝ ስሜት ታላቅ ኩራት ነው ያለችው ጋዜጠኛዋ ሁላችንም ለኢትዮጵያ የምንችለውን ሁሉ የማድረግ ግዴታ አለብን ማለቷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል::

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም