ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ አዲስ አበባ ገባች - ኢዜአ አማርኛ
ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ አዲስ አበባ ገባች

ታህሳስ 27 ቀን 2014 (ኢዜአ) ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትደርስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ሀላፊዎችና ሌሎች እንግዶች አቀባበል አድርገውላታል።
በአቀባበሉ ላይ አትሌት ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴም ተገኝቷል።
ጋዜጠኛዋ ኑሮዋን በአሜሪካ አድርጋ በኢትዮጵያ ላይ ሲደረግ የነበረውን ኢ-ፍትሀዊ አካሄድ ስትቃወም መቆየቷ ይታወቃል።
ሔርሜላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡትን ጥሪ ተቀብለው እየመጡ ከሚገኙ ዳያስፖራዎች መካከል ናት።
ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አሜሪካዊ ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ የ’በቃ’ ወይም ‘#NoMore’ ዘመቻን በማስተባበርና የኢትዮጵያን እውነት ለዓለምአቀፉ ማህበረሰብ የማስረዳት ተግባር እያከናወነች ትገኛለች።