የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርትራ ገቡ

106

ታህሳስ 26 ቀን 2014 (ኢዜአ) የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ዛሬ ኤርትራ ገቡ።

ቻይና ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ጉብኝት በሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በኩል በአዲሱ አመት መግቢያ የሚካሄድ ሲሆን ውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩ በኤርትራ፣ ኬንያ፣ ኮሞሮስ፣ ማልዲቭስ እና ሴሪላንካ እንደሚጋጓዙ መገለጹ ይታወሳል።

በዚሁ መሰረት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዋንግ ዪ የተመራ ልዑክ ዛሬ አስመራ ገብቷል።

ዋንግ ዩ እና ልዑካቸው አስመራ ኤርፖርት ሲደርሱ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል እንዳደረጉላቸው የሀገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል አስታውቀዋል።

በኤርትራ በሚኖራቸው ቆይታ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር እንደሚወያዩ ሚኒስትሩ የማነ ገብረ መስቀል ገልጸዋል።ባለፈው ወር የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ኢትዮጵያን መጎብኘታቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም