መቄዶኒያ በአሸባሪው ህወሃት ወረራ ለተፈናቀሉ ወገኖች 20 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የአይነት ድጋፍ ላከ

74

ታህሳስ 26/2014/ኢዜአ/ መቄዶኒያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በአሸባሪው ህወሃት ወረራ ለተፈናቀሉ ወገኖች 20 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የአይነት ድጋፍ ላከ።
የማዕከሉ መስራችና ሰራ አስኪያጅ የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ፤ ''እኛም ደጋፊ የምናገኘው ኢትዮጵያ ስትኖር በመሆኑ" ለተቸገሩ ወገኖች ድጋፍ ልከናል ብለዋል።

አሁን ላይ ተቸግረው የምናግዝቸው ወገኖች በቀጣይ ከራሳቸው አልፈው እኛን የሚረዱን በመሆናቸው ከተለገሰልን ቀንሰን ለመለገስ በማሰብ 20 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የአይነት ድጋፍ ልከናል ነው ያሉት።

"ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው'' በሚለው መርህ መሰረት ችግረኞችን ለመርዳት መንቀሳቀሳቸውን ጠቅሰዋል።

በመሆኑም የተቸገሩ ወገኖችን በማገዝና በመደገፍ ሁሉም የሚችለውን በማድረግ አለኝታነቱን እንዲያሳይ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

መቄዶኒያ ዛሬ ያደረገው ድጋፍ በዋግህምራ ለተፈናቀሉ ዜጎች ተደራሽ እንደሚሆን ጠቁመው በቀጣይ በአፋርና አማራ ክልሎችም መሰል ድጋፎችን ያደርጋል ብለዋል።

መቄዶኒያ በአሁኑ ወቅት ከ7 ሺህ በላይ አረጋዊያንና የአእምሮ ህሙማንን እየረዳ ያለ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም