በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ እና ሀይቅ ከተሞች ትምህርት ተጀምሯል

ታህሳስ 26 ቀን 2014 (ኢዜአ)በህወሓት የሽብር ቡድን ወረራ ምክንያት በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ እና ሀይቅ ከተሞች ከሁለት ወር በላይ ተቋርጦ የቆየው ትምህርት በድጋሚ ተጀምሯል።

በሁለቱም ከተሞች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ መደበኛ ትምህርት ተጀምሯል።

የሀይቅ ከተማ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ያሬድ ጌታቸው በአሸባሪው ህውሓት ወረራ ምክንያት ሁለት ወር ከ15 ቀን በኋላ በድጋሜ ትምህርት መጀመሩን ገልፀዋል።

ትምህርት ቤቶቹም ባለው ግብዕት መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደትን እያስቀጠሉ እንደሚገኙም ተናግረዋል።

ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎችም በትምህርት ቤቶች ተገኝተው ትምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ

‼️

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼️

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼️

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼️
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም