ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ የምታደርገው የነፃነት ትግል የመላ አፍሪካዊያን የፍትህና የነፃነት ትግል ተደርጎ መወሰድ አለበት

ታህሳስ 25/2014/ኢዜአ/ ኢትዮጵያ የምታደርገው የነፃነት ትግል የመላ አፍሪካዊያን የፍትህና የነፃነት ትግል ተደርጎ መወሰድ አለበት ሲል ደቡብ አፍሪካዊው የማህበረሰብ ንቅናቄ መሪ ሎንታታ ላክስ ገለፀ።

የአፍሪካ እናት ወደ ሆነችው ኢትዮጵያ በመምጣቴ ታላቅ ክብርና ደስታ ተሰምቶኛልም ብሏል።
በደቡብ አፍሪካ ስዌቶ የወጣቶች እንቅስቃሴ መሪ ሎንታታ ላክስ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብቷል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ እንዲሁም የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ፅጌሬዳ ዘውዱ በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት ለላክስ አቀባበል አድርገዋል።

This image has an empty alt attribute; its file name is nebu.jpg

የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኙ ላክስ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው #የበቃ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ ላይ ብቻ ሳይገደብ አህጉራዊ ሆኖ እንዲቀጥል ለማድረግና ልምዱን ለማካፈል መሆኑ ታውቋል።

ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው አስተያየትም "የምወዳትና የአፍሪካ እናት ወደ ሆነችው ኢትዮጵያ በመምጣቴ ታላቅ ክብርና ደስታ ተሰምቶኛል" ብሏል።

የ34 ዓመቱ ላክስ በደቡብ አፍሪካ ወጣቶችና የተለያዩ ተቋማት ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው ሲሆን ‘የአፍሪካውያን ችግር በአፍሪካውያን መፈታት አለበት’ የሚል ጽኑ አቋም አለው።

አፍሪካዊያን በህዝብ ድምጽ መመራት እንጂ በውጭ ተጽዕኖ ስር መውደቅ የለባቸውም ብሎ የሚያምነው ላክስ አንድነታቸውን በማጠናከር በትብብር የሚሰሩበት ወቅት አሁን ነው ብሏል።

በኢትዮጵያ ላይ አሁን አየደረሰ ያለውን የውጭ ጣልቃ ገብነትና ጫና ለመመከት መላ አፍሪካውያን በጋራ ሊቆሙ ይገባል ብሏል።

ኢትዮጵያ ክብሯንና ነፃነቷን ለማስጠበቅ እያደረገችው ያለው ትግል የመላ አፍሪካዊያን  የፍትህና የነፃነት ትግል ተደርጎ መወሰድ አለበት ብሏል።

ለኢትዮጵያ ብቻ ስንል አይደለም ከጎኗ የምንቆመው ለመላ አፍሪካዊያን ህልውና በማሰብ ነው ሲል መልእክቱን አስተላልፏል።

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንድታገኝ መሪዎች ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ወጣቶችም ጎን ለጎን ትግል ማድረግ እንደሚገባቸው አንስቷል።

የአፍሪካ እናት ወደ ሆነችው ኢትዮጵያ በመምጣቴ ታላቅ ክብርና ደስታ ተሰምቶኛልም ብሏል ላክስ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፤ የኢትዮጵያን ህልውና ለማስጠበቅ ወደ ግንባር ዘምተው ያሳዩትን ቆራጥ አመራር  የአፍሪካ ወጣቶች በአርአያነት ሊወስዱት ይገባል ብሏል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተወከሉት ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ፤ በ#NoMore ንቅናቄ ከኢትዮጵያ ጎን በመሆን በተለይም በደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ተሳትፎ ሲያደርግ መቆየቱን ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ፅጌሬዳ ዘውዱ፤ ኢትዮጵያ በውጭ ሃይሎች ከሚደረግባት ተጽዕኖ ጋር ተያይዞ ይህን ለመቋቋም የተጀመረውን #የበቃ  እንቅስቃሴ የበለጠ ለማጠናከር ደቡብ አፍሪካዊው የማህበረሰብ ንቅናቄ መሪ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት የጎላ አስተዋፆ እንደሚኖረው አንስተዋል።

This image has an empty alt attribute; its file name is gt.jpg

ላክስ በኢትዮጵያ በሚኖረው ቆይታ ከወጣቶች ጋር ተገናኝቶ ውይይት እንደሚያደርግ እና በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ተዘዋውሮ ጉብኝት እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

ደቡብ አፍሪካዊው የማህበረሰብ ንቅናቄ መሪ ላክስ አፍሪካዊያን ወጣቶች የውጭ ጫናዎችን እንዴት መቋቋም እንዳለባቸውና የጥፋት እቅድ ያለው ባዕድ ሃሳብ እንዳይገዛቸው የሚታገል ወጣት መሆኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም