‘ስለ ኢትዮጵያ’ በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ ለጉብኝት ክፍት ሆነ

14

ታህሳስ 25 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ‘ስለ ኢትዮጵያ’ በሚል ርዕስ ያዘጋጀው የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ ዛሬ ለጉብኝት ክፍት ሆኗል።

በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት በሚካሄደው አውደ ርዕይ መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ኢድሪስ፣የመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪያት የውጭ ቋንቋዎችና ዲጂታል ሚዲያ ሃላፊ ቢልለኔ ስዩም፣የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረትና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

አውደ ርዕዩ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ አገርን ለማዳን ያደረጉትን ተጋድሎ የሚታይበት እንደሆነ ተገልጿል።

May be an image of 9 people and people standing

በትግራይ ክልል የአገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ከሕዝቡ ጋር የነበረው መስተጋብርና ያበረከተው አስተዋጽኦ፣ የደረሰበት ጥቃትና ጉዳት እንዲሁም አገርን ለማዳን የከፈለውን መስዋዕትነት የሚሳዩ ፎቶዎች በአውደ ርዕዩ ላይ ይታያሉ ተብሏል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለአገር መከላከያ ሰራዊት ያደረገው ድጋፍ እንዲሁም አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በአማራና አፋር ክልሎች ፈጽሞት በነበረው ወረራ በዜጎች ላይ ያደረሰውን አሰቃቂ ድርጊቶችና በተለያዩ ተቋማት ላይ ያደረሰውን ከፍተኛ ውድመትና ዝርፊያ የሚያሳዩ ፎቶዎች ለሕዝብ እይታ ይቀርባሉ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ‘ስለ ኢትዮጵያ’ በሚል ርዕስ ያዘጋጀው የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ እስከ ጥር 12 ቀን 2014 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን፤ኢትዮጵያውያን፣ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት፣ የውጪ አገር ዜጎች፣ ዲፕሎማቶችና ሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎች ይጎበኙታል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም