በደቡብ አፍሪካ ስዌቶ የወጣቶች እንቅስቃሴ መሪ ሎንታታ ላክስ አዲስ አበባ ገባ

24

ታህሳስ 25 ቀን 2014 (ኢዜአ) በደቡብ አፍሪካ ስዌቶ የወጣቶች እንቅስቃሴ መሪ ሎንታታ ላክስ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገባ።

የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ ወጣቱ ላክስ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው #የበቃ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ ላይ ብቻ ተገድቦ እንዳይቀርና ዘላቂነት እንዲኖረው ለማድረግና ያለውን ልምድ ለማካፈል ነው።

በተለይ አፍሪካዊያን ወጣቶች የውጭ ጫናዎችን እንዴት መቋቋም እንዳለባቸውና ባዕድ ሀሳብ እንዳይገዛቸው የሚታገል ወጣት ነው።

ላክስ በደቡብ አፍሪካ ወጣቶችና የተለያዩ ተቋማት ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው ሲሆን ‘የአፍሪካውያን ችግር በአፍሪካውያን መፈታት አለበት’ የሚል ጽኑ አቋም አለው።

ላክስ ወደሚወዳት የአፍሪካ እናት ኢትዮጵያ በመምጣቱ የተሰማውን ደስታ ገልጿል።

ላክስ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የጠቅላይሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተወካይ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ፅጌሬዳ ዘውዱ ተቀብለውታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም