ወደአገር ቤት የገባ የዳያስፖራ ቡድን በወራሪው ኃይል የተጎዱ አካባቢዎችን ለመመልከት ወደ አፋርና አማራ ክልሎች አቀና - ኢዜአ አማርኛ
ወደአገር ቤት የገባ የዳያስፖራ ቡድን በወራሪው ኃይል የተጎዱ አካባቢዎችን ለመመልከት ወደ አፋርና አማራ ክልሎች አቀና
ታህሳስ 24 ቀን 2014 (ኢዜአ) የእናት አገር ጥሪን ተከትሎ ወደ አገር ቤት የገባ የዳያስፖራ ቡድን በአሸባሪው ህወሃት ወረራ የተጎዱ አካባቢዎችን ለመመልከት ወደ አፋርና አማራ ክልሎች አቅንቷል።
ከውጭ አገራት የገቡ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የአማራና አፋር አካባቢዎችን ለመጎብኘት ዛሬ ጠዋት ከአዲስ አበባ ወደ አፋር አቅንተዋል።
በጉዟቸው ከአፋር ጀምሮ ወደ አማራ ክልል በመቀጠል ጉብኝቱን ያካሂዳሉ።
በነገው ዕለት ውሎ በአፋር ሰመራ ከተማ ሲምፖዚየም እንደሚኖርም ይጠበቃል።