የአፄ ቴዎድሮስ ቁንዳላ (ሹርባ) የሽኝት ፕሮግራም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የአፄ ቴዎድሮስ ቁንዳላ (ሹርባ) የሽኝት ፕሮግራም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

ታህሳስ 24 ቀን 2014 (ኢዜአ)የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ቁንዳላ (ሹርባ) እና ሌሎች የመቅደላ ታሪካዊ ቅርሶች ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር የሽኝት ፕሮግራም እየተደረገላቸው ነው።
በሽኝት መርሃግብሩ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ ሌሎች የፌደራልና የአዲስ አበባ ባለስልጣናት፣ ጀግኖች አርበኞች፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎችና ሌሎችም የሽኝት መርሃግብሩ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።
የንጉሡ ቁንዳላ ወደ ጎንደር የሚሄደው ለህዝብ እይታ ለመቅረብ ሲሆን በዛሬው ዕለት በጎንደር ከተማ ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግለት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ገልጿል።
ከ150 ዓመታት በኋላ ወደ ሀገር ቤት ተመልሶ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም መቆየቱ ይታወሳል።