ቀጥታ፡

ኒጀር በጸጥታው ምክር ቤት ፕሬዝዳንትነቷ ለአፍሪካ ድምጽ ሆናለች

ታህሳስ 23 ቀን 2014 (ኢዜአ) ኒጀር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጸጥታው ምክር ቤት ፕሬዝዳንትነቷ ለአፍሪካ ድምጽ ሆናለች ሲሉ በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ገለጹ።

ኒጀር የእ.አ.አ 2021 ታህሳስ ወር የምክር ቤቱ ፕሬዘዳንት ሆና መርታለች።በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ኒጀር የጸጥታው ምክር ቤት ፕሬዝዳንትነቷን በስኬት በማጠናቀቋ እንኳን ደስ አለሽ ማለት ያስፈልጋል ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።

ኒጀር በቆይታዋ ለአፍሪካ በጣም ወሳኝ ድምጽ መሆኗን አመልክተዋል።ወደ ጸጥታው ምክር ቤት ምክንያታዊነትና ጥበብ የተሞላበት አካሄድ ይዛ መምጣቷንም ነው አምባሳደር ታዬ የገለጹት።

ኖርዌይ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ወርሃዊ ፕሬዝዳንትነትን ከኒጀር ተረክባለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም