ምክር ቤቱ የክልሉን የዐሥር ዓመት መሪ ዕቅድና የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አጸደቀ

51

ሀዋሳ ታህሳስ 22 ቀን 2014 (ኢዜአ) የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ስድስተኛ ዙር አንደኛ የሥራ ዘመን አንደኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬ ውሎው የክልሉን የዐሥር ዓመት መሪ ዕቅድና የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ ተወያይቶ አፅድቋል ፡፡

የስድስተኛ ዙር መስራች ጉባኤ ቃለ ጉባኤ በማፅደቅ የዛሬ ውሎውን የጀመረው ምክር ቤቱ በክልሉ የዐሥር ዓመት መሪ ዕቅድና የክልሉ መንግስት የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ሰፊ ውይይት አካሂዶ አፅድቋል ፡፡

በውይይቱ በ2014 በጀት ዓመትም ሆነ በቀጣይ 10 ዓመታት የክልሉን ህዝብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሥራዎች ላይ ትኩረት መሰጠት እንደሚገባ አጽእኖት ተሰጥቷል፡፡

በክልሉ ልማትና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በከፍተኛ ድርሻና ሀላፊነት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተመላለክቷል ፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም