የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ እየተወያዩ ነው

37

አሶሳ ፤ታሳስ 22 / 2104(ኢዜአ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ክልላዊና ሃገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በአሶሳ ከተማ እየተወያዩ ነው።

የብልፅግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ኢስሃቅ አብዱቃድር ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ የድህረ ጦርነት መዛነፎች እና እርምቶች በሚል ሰነድ ላይ ውይይት ያደርጋሉ፡፡

ዓላማው በህልውና ዘመቻው የተገኙ ድሎችን በማስቀጠል የክልሉን ብሎም የሀገሪቱን ብልጽግና ማረጋገጥ የሚያስችል አቅጣጫ ለማስቀመጥ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት በሚቆየው የውይይቱ መድረክ ከ150 በላይ የክልል፣ ዞን እና ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡

ከውይይቱ በኋላ የተደረሰበትን ውጤት ለህብረተሰቡ ይፋ እንደሚደረግ አቶ ኢስሃቅ አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም