የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና የብሉናይል ግዛት በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

67

ታህሳስ 21 ቀን 2014 (ኢዜአ)የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና የብሉናይል ግዛት ከዚህ ቀደም የነበራቸውን ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ዛሬ ተፈራርመዋል፡፡

በአሶሳ ከተማ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው በኢትዮጵያ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና በሱዳን የብሉናይል ግዛት የጋራ የድንበር ልማት ትብብር ውይይት ተጠናቋል፡፡

በውይይቱ ማጠናቀቂያም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና የብሉናይል ግዛት በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ እንዲሁም በሠላም፣ በልማት፣ በህዝብ ግንኙነት ዘርፎች በቀጣይ በጋራ በሚከናወኑ ሥራዎች ዙሪያ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን እና የብሉናይል ግዛት ፕሬዚዳንት ጀነራል አህመድ አልዑምዳ ናቸው የፈረሙት።

ስምምነቱን በተፈራረሙበት ወቅት በልማት፣በሕዝብ ግንኙነት በሠላም እና ሕዝቦችን ተጠቃሚ በሚያደርጉ በሌሎች መሠል ጉዳዮች በጋራ ከመስራት ባለፈ፣ አፈጻጸሙን በየጊዜው እየተገናኙ እንደሚገመግሙም ገልፀዋል፡፡

ስምምነቱን በጋራ ተግባራዊ በማድረግ የሁለቱን ሀገራት ክልሎች ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከርና ሕዝብን ተጠቃሚ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ መናገራቸውን ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ

‼️

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼️

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼️

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼️
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም