ኮሎኔል መንግስቱ የምህረት አዋጁ የማይመለከታቸው መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
ኮሎኔል መንግስቱ የምህረት አዋጁ የማይመለከታቸው መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ገለጹ
አዲስ አበባ ነሐሴ 19/2010 ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም በአዋጁ መሰረት ይቅርታ የማይደረግላቸው መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አመለከቱ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ከጋዜጠኞች ለተነሳላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። በቅርቡ የወጣው የምህረት አዋጅን መሰረት አድርጎ የቀድሞ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱን ይመለከታቸዋል ወይ? በሚል ለተነሳላቸው ጥያቄ የምህረት አዋጁ የማይመለከታቸው እንደሆነ ገልጸዋል። ህገመንግስቱ የቀይ ሽብር ጉዳይ በምህረት አዋጅ የማይካተት መሆኑን ያስቀመጠ በመሆኑና የምህረት አዋጁ ከህገመንግስቱ በታች በመሆኑ ኮሎኔል መንግስቱ ምህረቱ የማይመለከታቸው እንደሆነ ገልጸዋል። የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ለ17 አመታት አገሪቱን ሲመሩ ቆይተው የደርግ መንግስት ሲወድቅና ኢህአዴግ አገሪቱን ሲቆጣጠር ወደዚምባቡዌ መኮብለላቸው ይታወቃል።