50 በመቶ ሜጋ ፕሮጅክቶች በቅርብ ወራት ይጠናቀቃሉ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ - ኢዜአ አማርኛ
50 በመቶ ሜጋ ፕሮጅክቶች በቅርብ ወራት ይጠናቀቃሉ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
አዲስ አበባ ነሐሴ 19/2010 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በግንባታ ላይ ከሚገኙ ፕሮጀክቶች ውስጥ 50 በመቶዎቹ በቅርብ ወራት እንደሚጠናቀቁ ተናገሩ። መንግስት ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ትኩረት መስጠቱንም አረጋግጠዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት የታላቁ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ በሌሎች ፕሮጀክቶች አፈጻጸም መጓተት እንደ ሜቴክ አይነት ልምድ የሌላቸው ድርጅቶች ምክንያት መሆናቸውን አንስተዋል፡፡ የፕሮጀክት አስተዳደርና ዲዛይን ችግርም ለመጓተታቸው ተጨማሪ ምክንያት መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ቢያንስ 50 በመቶ ፕሮጀክቶች እንደሚጠናቀቁም ነው ያረጋገጡት። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ሞት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግድቡ ግንባታ ላይ ካደረጉት ንግግር ጋር የተገናኘ እንደሁ ለተጠየቁት ጥያቄም ኢንጂነር ስመኘው በመስኩ ልምድና ብቃት ያለው የመንግስት ሰራተኛ እንጂ ኮንትራት የወሰደ አካል ባለመሆኑ ከንግግራቸው ጋር እንደማይያያዝ ተናግረዋል፡፡ በዚህም በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ ባለው አፈጻጸም ልምድ ያላቸው ኩባንያዎች ገብተው አንዲሰሩና የኢንጂነሩን የበረሃ ቆይታ የሚቀንስ እንጂ ኢንጂነሩን የሚጎዳ አይደለም ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የነበሩትን እያፈረሱ አዲስ ይገነባሉ” ተብሎ ለቀረበላቸው ሃሳብም ባለፉት 20 ዓመታት የተሰሩ ጥፋቶችና ድሎች የጋራ ናቸው የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ባለፉት ዓመታት በልማትና በዴሞክራሲ ያስገኘናቸው ውጤቶች የኢትዮጵያ ህዝብ ድሎች ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለነበሩ ክፍተቶች ግን አንደ መንግስት ኃላፊነት መውሰድ እንጂ ድል የመቀራመት ጉዳይ መሆን የለበትም ነው ያሉት። የተሰሩ መልካም ስራዎችን ማፍረስ ሳይሆን “በተሰጠኝ ኃላፊነት የራሴን አስተዋጽኦ አበርክቼ ማለፍ ነው ፍላጎቴ” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
በኢንቨስትመንት ረገድም ለወጭ ባለሀብቶች የሚሰጠው የታክስ እፎይታና ወደውጭ የሚልኩት ምርት ተመጣጣኝ ያለመሆኑ ችግር እስከመቸ ይቀጥላል ለሚለው ጥያቄ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የውጭ ቀጥታ ኢንቨሰትመንት መረጣና አሰትዳደር ላይ መስራት እንጂ ሰፋፊ ኢንቨስትመንት ላይ ገና ብዙ መስራት እንደሚጠበቅ ነው ያብራሩት። በአገር ውስጥ ኢንቨስትመንት ላይም በዕውቀት፣ በአስተሳስብና በገንዘብ ድጋፍ ማድረግ፣ አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ ማስቻል እንደሚገባም ገልጸዋል። ከተሸከርካሪ ጋር በተያያዘ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያም ሀገሪቱ በየዓመቱ ለነዳጅ ወጪ ከ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደምታወጣ ገልጸው ይህም ተሸከርካሪ በገፍ ማስገባቱ ችግሩን እንደሚያባብሰው ተናግረዋል፡፡ የሀገሪቱ የመንገድ መሰረተ ልማትም ይህን ፍላጎት የሚያስተናግድ አለመሆኑን ነው ያብራሩት፡፡
ከስደት ጋር በተያያዘ ስደትን መቀነስ እንጂ ማስወገድ አይቻልም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ስደትን መቀነስ በሚቻልባቸው በስራ ፈጠራና በኢኮኖሚው ጉዳዮች ላይ እንደሚሰራ፣ በስደት ላይ ለሚገኙ ወገኖችም መብታቸው እንዲከበር ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንደሚደረግ ተናግረዋል። ከኤርትራ ጋር የተፈጠረውን ሰላም ተከትሎ ቀጥታ ድጋፍ ሲያደርጉ ያልነበሩ ተቋማትና አገራት ድጋፍ ማድረግ መጀመራቸውን ገልጸው፤ ለአብነትም በቀጥታ በጀት ድጋፍ አድርጎ የማያውቀው ዓለም ባንክ በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት አንድ ቢሊዮን ዶላር በካፒታል በጀት ሊሰጥ እንደሚችል ጠቅሰዋል። በእድገት ብቻ የሰውን አዳዲስ ፍላጎት መገደብ እንደማይቻል በመግለጽም፤ ሰላምን በማስፈን አሰቃቂ የስደት ድርጊትን መቀነስ እንደሚቻል ነው ያብራሩት። በሼክ አሊ አላሙዲ ጉዳይም ሳዑዲ በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞን መፍታቷን ገልጸው፤ ሼህ አሊ አላሙዲንን ለመፍታት ቃል ብትገባም በአገሪቱ ያለው የህግና አስተሳስብ ውስብስብ ችግር ምክንያት መዘግየቱን ተናግረዋል። ባለሀብቱ የሳዑዲ ዜግነት ያላቸው በመሆናቸው እንዲፈቱ ማስገደድ አይቻልም ያሉት ጠቅላይ ሚኒሰትሩ፤ ጉዳዩን እየተከታተሉ መሆኑን ገልጸው ምናልባትም ከተሳካ በቅርቡም እናያቸዋለን ብለን እንጠብቃለን ብለዋል። የኢትጵያ ሶማሌ ፕሬዝዳንት ጉዳይም ህግ የሚወስነው ጉዳይ በመሆኑ ወደፊት ይታያል ብለዋል። ሌሎች ስልጣናቸውን በአግባቡ ያልጠተቀሙ ግለሰቦችም በህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ አረጋግጠዋል። በ2030 ዓ.ም ምን እንጠበቅ ለተባሉትም ባለን የተማረ ኃይል፣ ባለን ተፈጥሯዊ ሀብት ከተጠቀምን፣ ዴሞክራሲ ካሰፋን በ2030 ምርጥ ኢትዮጵያን እጠብቃለሁ ብለዋል።