ለኢትዮጵያና ኤርትራ ሰላምና አንድነት መረጋገጥ ሁሉም የበኩሉን ኃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አሳሰቡ - ኢዜአ አማርኛ
ለኢትዮጵያና ኤርትራ ሰላምና አንድነት መረጋገጥ ሁሉም የበኩሉን ኃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አሳሰቡ
አዲስ አበባ ነሐሴ 19/2010 በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የተፈጠረው ሰላምና አንድነት ቀጣይነት ለማረጋገጥ ሁሉም የበኩሉን ኃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አሳሰቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅታዊና በልዩ ልዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ከመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጋር የተገናኙ ሲሆን ውይይት ያደረጉትም ቁጥራቸው 120 ከሚሆኑ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጋር ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በሰጡት ምላሽም፤ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ሰላምና አንድነት እንዲመጣ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የበኩላቸውን ሲወጡ መቆየታቸውን ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የተፈጠረው ሰላምና አንድነት ቀጣይነት ለማረጋገጥ ሁሉም የበኩሉን ኃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት። ዶክተር አብይ አሕመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተሾሙበት ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም በኋላ ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች ማብራሪያ ሲሰጡ ይህ የመጀመሪያቸው ነው።