ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላል ይበላ አብያተክርስቲያናትን እና ገዳማትን ተመለከቱ - ኢዜአ አማርኛ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላል ይበላ አብያተክርስቲያናትን እና ገዳማትን ተመለከቱ

ታኅሣሥ 10 ቀን 2014 (ኢዜአ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላል ይበላ አብያተክርስቲያናትን እና ገዳማትን ተመልክተዋል።
ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋር የሰላም ሚኒስተሩ ብናልፍ አንዱዓለም፣ ከፍተኛ የጦር ጀኔራችና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ደብረ ሮሃ ቅዱስ ላል ይበላን ተመልክተዋል።

አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በቅድስቲቱ ከተማ ላል ይበላ በነበረበት ወቅት በነዋሪዎች ላይ በደሎችን ሲፈፅም እንደነበር ተገልጿል።
የገዳማቱንና አብያተክርስቲያናቱን አገልጋይ ካሕናትንም ልብሰ ተክሕኖአቸውን በማስወለቅ ያንገላቷቸው እንደነበር መነገሩን የአሚኮ ዘገባ አመልክቷል።