በወልዲያ ከተማ አምስት ለፍቶ አዳሪዎች እንዲንበረከኩ ተደርጎ ጥይት በእሩምታ ተጨፍጭፈዋል

ታህሳስ 10 ቀን 2014 (ኢዜአ) በወልዲያ ከተማ ውሀ ለመቅዳት ወንዝ የወረዱ አምስት ለፍቶ አዳሪዎች በሰልፍ እንዲንበረከኩ ተደርጎ በጥይት እሩምታ ተጨፍጭፈዋል።

የወልድያ ከተማ ነዋሪዎች የጨለማ ጊዜ ያሳለፉት በመብራት እጦት ብቻ ሳይሆን በሚደርስባቸው መከራና ግፍ ጭምር ነበር።

የከተማዋ ነዋሪ የሆነችው የአይን እማኝ አቶ አስራት የተባለን ግለሰብ ውሀ ቀድቶ ሲመለስ የአሸባሪው ህወሃት ታጣቂዎች በአደባባይ በጥይት ደብድበው ሲገድሉት አይቻለሁ ብላለች።

ሟች ከመኖሪያ ቤቱ ወጣ ብሎ ከሚገኝ ወንዝ ውሀ በጀሪካን ቀድቶ ሲመለስ መንገድ ላይ አስቆሙት፣ የተሸከመውን ጀሪካን አስወርደው አንበረከኩት፣ መታወቂያውን እያሳየ አትግደሉኝ የልጆች አባት ነኝ እያለ ቢማጸናቸውም ጆሮ ሳይሰጡት ህይወቱን እንደቀጠፉት ማየቷን ገልጻለች።

ይህ ብቻ አይደለም ዉሀ ለመቅዳት ወንዝ ሄደው ሲመለሱ ያገኟቸውን ሰዎች በሰልፍ አንበርክከው ግፍ በተሞላበት አኳኋን ጥይት አርከፍክፈው መግደላቸውን መመልከቷን ተናግራለች።

የሟች አቶ አስራት ባለቤትም የትዳር አጋራቸውና የልጆቻቸው አባት በአደባባይ መረሸን ጥልቅ ሃዘን እንደጣለባቸው ገልጸው፤ ቀጣይ የቤተሰባቸው ህይወት አስከፊ አደጋ ላይ መውደቁን ተናግረዋል።

የሟች ወንድምም እንደ እናትና አባት ሆኖ ያሳደገኝን ወንድሜን አልቅሰን እንኳን እንዳንቀብር ተከልክለናል ብለዋል።

_ አካባቢህን ጠብቅ፣

_ ወደ ግንባር ዝመት፣

_ መከላከያን ደግፍ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም